Directory

ውክፔዲያ - ሼክስፒር Jump to content

ሼክስፒር

ከውክፔዲያ
ዊሊያም ሼክስፒር

ዊሊያም ሼክስፒር (ታህሳስ ወር 1564 - ታህሳስ 23 ቀን 1616 እ.ኤ.አ.) በብዙወች ዘንድ ታላቁ የእንግሊዝኛ ጸሃፊ ተብሎ የሚገመት በእንግሊዝ አገር የኖረ ገጣሚተውኔት ደራሲድራማ አዘጋጅ ነበር። አብዛኛው ተውኔቶቹ ትራጄዲንና ታሪክን የተመረኮዙ ነበሩ። የኮሜዲ ጽሁፎችንም አቅርቧል። የግጥሞቹና ተውኔቶቹ አንኳር ሃሳቦች የሚያጠነጥኑት የፍቅርቅናትንዴትና መሰል ጠንካራ ስሜት ያለው ሰው ሰው ስለመሆን ናቸው። ሼክስፒር ጽሁፎቹን የመዘገባቸው በ1590 እና 1613 እ.ኤ.አ. መካከል ነበር።

ስለሼክስፒር ህይወት ብዙ የተመዘገበ ባይኖርም ሚስቱ አና ሃዘዋይ ትባል እንደነበርና ከርሱ በ5 ወይም 6 አመት ትበልጠው እንደነበር ይነገራል። ሼክስፒር 3 ልጆች ነበሩት፣ ሱዛና ሆል፣ ሃምነት ሼክስፒርና ጁዲት ቅኔይ ።[1]1592 እ.ኤ.አ. ሼክስፒር ተዋናይ የነበረ ሲሆን፣ በዚሁ ወቅት በተውኔት ደራሲነቱ እውቅናን እያተረፈ የመጣበት ዘመን ነበር። በ1616 እ.ኤ.አ. ሲሞት ሼክስፒር አንዳቸውንም ጽሁፉን አላሳተመመ ነበር፣ ምክንያቱም አይታወቅም። ተውኔቶቹ የታተሙት ከሞተ በኋላ ነበር።

የሼክስፒር ታዋቂ ጽሁፎች

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የጠፉ ጽሁፎች

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

"ሼክስፕሪርን" ማን ጻፈው?

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ሼክስፕሪ ከሞተ 150 ዓመት በኋላ ድርሰቶቹን እርሱ አልጻፋቸውም የሚል አስተያየት ብቅ አለ። ለዚህ ምክንያቱ ሼክስፒር ከእንግሊዝ ውጭ ብዙ ስላልተዘዋወረና በድርሰቶቹ ደግሞ ሌሎች አገሮችን፣ ለምሳሌ ጣሊያንን፣ ስፔንን ወዘተ በጥልቅ እንደሚዋቅ ስለሚያሳይ ነበር። ብዙ ተመራማሪወች የሼክስፒርን ድርሰቶች ሼክስፒር እንደጻፋቸው ቢያምንም አሁን ድረስ እርሱ አልጻፈውም የሚል ክርክር ይነሳል።

  1. ^ Koontz Terri፣ Mark Sidwell, World Studies for Christian Schools፣ Bob Jones University Press Greenville, South Carolina፣ pages 59