Directory

ውክፔዲያ - «የሰብዓዊ መብት አቀፋዊ መግለጽ» Jump to content

«የሰብዓዊ መብት አቀፋዊ መግለጽ»

ከውክፔዲያ
Eleanor Roosevelt & የሰብዓዊ መብት አቀፋዊ መግለጽ (1949)

ስለሰብአዊ መብቶች ለማስተማር የሚረዱ አንዳንድ ዘዴዎች።

በዩኔስኮ ተዘጋጅቶ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ኮሚሽን ተተረጎመ

የሰው ልጅ ሁሉ ሲወለድ ነጻና በክብርና በመብትም እኩልነት ያለው ነው። የተፈጥሮ ማስተዋልና ሕሊና ስላለው አንዱ ሌላውን በወንድማማችነት መንፈስ መመልከት ይገባዋል።
እያንዳንዱ ሰው የዘር የቀለም የጾታ የቋንቋ የሃይማኖት የፖለቲካ ወይም የሌላ ዓይነት አስተሳሰብ የብሔራዊ ወይም የኀብረተሰብ ታሪክ የሀብት የትውልድ ወይም የሌላ ደረጃ ልዩነት ሳይኖሩ በዚሁ ውሳኔ የተዘረዘሩት መብቶችንና ነጻነቶች ሁሉ እንዲከበሩለት ይገባል።
ከዚህም በተቀረ አንድ ሰው ከሚኖርበት አገር ወይም ግዛት የፖለቲካ የአገዛዝ ወይም የኢንተርናሽናል አቋም የተነሳ አገሩ ነጻም ሆነ በሞግዚትነት አስተዳደር ወይም እራሱን ችሎ የማይተዳደር አገር ተወላጅ ቢሆንም በማንኛውም ዓይነት ገደብ ያለው አገዛዝ ሥር ቢሆንም ልዩነት አይፈጸምበትም።
እያንዳንዱ ሰው የመኖር፣ በነጻነትና በሰላም የመኖሩ መጠበቅ መብት አለው።
ማንም ሰው ቢሆን በባርነት አይገዛም። ባርነትና የባሪያ ንግድም በማንኛውም ዓይነት ክልክል ነው።
ማንም ሰው ቢሆን የጭካኔ ስቃይ እንዳይደርስበት ወይም ከሰብዓዊ አፈጻጸም ውጭ የሆነ የተዋረድ ተግባር ወይም ቅጣት አይፈጸምበትም።
እያንዳንዱ ሰው በሕግ ፊት በሰው ዘርነቱ የመታወቅ መብት አለው።
ሰው ሁሉ በሕግ ፊት እኩል ነው። ያለአንዳች ልዩነትም ሕጉ ደህንነቱን እንዲጠበቅለት እኩል የሆነ መብት አለው። ይህንን ውሳኔ በመጣስ ከሚደረግ ልዩነት ለማድረግ ከሚነሳሳ እንዲጠበቅ ሁሉም የእኩል መብት አለው።
እያንዳንዱ ሰው በሕገ መንግስቱ ወይም በሕግ የተሰጡትን መሠረታዊ መብቶች ከሚጥሱ ድርጊቶች ከፍተኛ በሆኑ ብሔራዊ የፍርድ ባለስልጣኖች ፍጹም በሆነ መንገድ እንዲወገድለት መብት አለው።
ማንም ሰው ያለፍርድ ተይዞ እንዲታሰር ወይም በግዛት እንዲኖር አይደረግም።
እያንዳንዱ ሰው በመብቶቹና በግዴታዎቹ አፈጻጸም እንዲሁም በሚከሰስበት ማንኛውም ዓይነት የወንጀል ክስ ነጻ በሆነና በማያዳላ የፍርድ ሸንጎ በትክክለኛና በይፋ ጉዳዩ እንዲሰማለት የሙሉ እኩልነት መብት አለው።

አንቀጽ ፲፩፤

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
፩/፡ በወንጀል ክስ የተከሰሰ ማንኛውም ሰው ለመከላከያው አስፈላጊዎች የሆኑትን ሁሉ አቅርቦ በሚከራከርበት የይፋ ፍርድ ቤት በሕግ መሠረት ወንጀለኛ መሆኑ እስቲረጋገጥበት ድረስ ከወንጀል ነጻ እንደሆነ የመቆጠር መብት አለው።
፪/፡ ማንም ሰው በብሔራዊ ወይም በኢንተርናሽናል ሕግ አንድ ነገር ወንጀል ሆኖ ባልተደነገገበት ጊዜ በፈጸመው ወይም ባልፈጸመው ማንኛውም ሥራ ወንጀለኛ ሆኖ አይከሰስም። ወይም ወንጀሉ በተፈጸመበት ጊዜ ከተደነገገው ቅጣት ይበልጥ አይፈረድበትም።

አንቀጽ ፲፪፤

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
ማንም ሰው በግል ኑሮው በቤተሰቡ ውስጥ በቤቱ ወይም በሚጻጻፈው ደብዳቤ በፍርድ ያልተለየ ጣልቃ ገብነት ወይም ክብሩን የሚነካና ስሙን የሚያጎድፍ ተቃውሞ አይፈጸምበትም። እያንዳንዱ ሰው ከእንደዚህ ያለ ጣልቃ ገብነት ወይም የሚጎዳ ተግባር ሕግ እንዲከላከልለት መብት አለው።

አንቀጽ ፲፫፤

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
፩/፡ እያንዳንዱ ሰው በየብሔራዊ ወሰን ክልሉ የመዘዋወርና የመኖር ነጻነት መብት አለው።
፪/፡ እያንዳንዱ ሰው ከማንኛውም አገር ሆነ ከራሱ አገር ወጥቶ እንደገና ወደ አገሩ የመመለስ መብት አለው።

አንቀጽ፡፲፬፤

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
፩/፡ እያንዳንዱ ሰው ከጭቆና ሸሽቶ በሌሎች አገሮች ጥገኝነትን የመጠየቅና በደህና የመኖር መብት አለው።
፪/፡ ፖለቲካዊ ካልሆኑ ወንጀሎች ወይም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ዓላማዎችን ከሚቃረኑ ሥራዎች የተነሳ በሚደርሱ ክሶች ምክንያት ከሆነ ይህ መብት ሊያገለግል አይችልም።

አንቀጽ፡፲፭፤

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
፩/፡ እያንዳንዱ ሰው የዜግነት መብት አለው።
፪/፡ ማንም ሰው ያለፍርድ ዜግነቱ አይወሰድበትም ወይም ዜግነቱን የመለወጥ መብት አይነፈገውም።

አንቀጽ፡፲፮፤

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
፩/፡ አካለ መጠን የደረሱ ወንዶችና ሴቶች በዘር በዜግነት ወይም በሃይማኖት ልዩነት ሳይወሰኑ ጋብቻን የመፈጸምና ቤተሰብን የመመሥረት መብት አላቸው፤ ጋብቻ በመፈጸም በጋብቻ ጊዜና ጋብቻ በሚፈርስበትም ጊዜ እኩል መብት አላቸው።
፪/፡ ጋብቻ የሚፈጸመው ጋብቻ ለመፈጸም በሚፈልጉ ሁለቱም ወገኖች በሚያደርጉት ነጻና ሙሉ ስምምነት መሠረት ብቻ ነው።
፫/፡ ቤተሰብ በኀብረ ሰብ የተፈጥሮና መሰረታዊ ክፍል ስለሆነ በኀብረሰቡና በመንግሥቱም ደህንነቱ እንዲጠበቅለት ይገባል።

አንቀጽ፡፲፯፤

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
፩/፡ እያንዳንዱ ሰው ብቻውን ወይም ከሌሎች ጋር በኀብረት ሆኖ የኀብረት ባለቤትነት መብት አለው።
፪/፡ ማንም ሰው ያለፍርድ ንብረቱ አይወሰድበትም።

አንቀጽ፡፲፰፤

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
እያንዳንዱ ሰው የሃሳብ የሕሊናና የሃይማኖት ነጻነት መብት አለው። ይህም መብት ሃይማኖቱን ወይም እምነቱን የመለወጥ ነጻነትንና ብቻውን ወይም ከሌሎች ጋር በኀብረት በይፋ ወይም በግል ሆኖ ሃይማኖቱን ወይም እምነቱን የማስተማር፣ በተግባር የመግለጽ የማምለክና የማክበር ነጻነትን ይጨምራል።

አንቀጽ፡፲፱፤

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
እያንዳንዱ ሰው የሐሳብና ሐሳቡን የመግለጽ መብት አለው። ይህም መብት ያለጣልቃ ገብነት በሐሳብ የመጽናትንና ዜናን ወይም ሐሳቦችን ያላንዳች የድንበር ገደብ የማግኘትን የመቀበልን ወይም የማካፈልን ነጻነትም ይጨምራል።

አንቀጽ፡፳፤

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
፩/፡ እያንዳንዱ ሰው በሰላም የመሰብሰብና ግንኙነት የማድረግ ነጻነት መብት አለው።
፪/፡ ማንም ሰው የአንድ ማኀበር አባል እንዲሆን አይገደድም።

አንቀጽ፡፳፩፤

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
፩/፡ እያንዳንዱ ሰው በቀጥታ ወይም ነጻ በሆነ መንገድ በተመረጡ እንደራሴዎች አማካኝነት በአገሩ መንግስት የመካፈል መብት አለው።
፪/፡ እያንዳንዱ ሰው በአገሩ የህዝብ አገልግሎት እኩል የማግኘት መብት አለው።
፫/፡ የመንግስት ሥልጣን መሠረቱ የሕዝቡ ፈቃድ መሆን አለበት። ይህም ፈቃድ ለሁሉም እኩል በሆነ በምሥጢር በሚደረግ የድምፅ መስጠት ምርጫ ወይም በተመሳሳይ ሁኔታ በየጊዜውና በትክክል በሚፈጸሙ ምርጫዎች እንዲገለጽ መሆን አለበት።

አንቀጽ፡፳፪፤

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

እያንዳንዱ፡ ሰው፡ የኀብረ፡ ሰብ፡ አባል፡ እንደመሆኑ፡ በኀብረ፡ ሰብ፡ ደህንነቱ፡ እንዲጠበቅ፡ መብት፡ አለው። እንዲሁም፡ በብሔራዊ፡ ጥረትና፡ በኢንተርናሽናል፡ መተባበር፡ አማካይነትና፡ በእያንዳንዱ፡ መንግስት፡ ድርጅትም፡ የሀብት፡ ምንጮች፡ መሰረት፡ ለክብሩና፡ ለሰብዓዊ፡ አቅሙ፡ ነጻ፡ እድገት፡ የግድ፡ አስፈላጊ፡ የሆኑት፡ የኤኮኖሚ፡ የማኀበራዊ፡ ኑሮና፡ የባህል፡ መብቶች፡ በተግባር፡ እንዲገለጹለት፡ መብት፡ አለው።

አንቀጽ፡፳፫፤

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

፩/፡ እያንዳንዱ፡ ሰው፡ የመሥራት፡ የሥራ፡ ነጻ፡ ምርጫና፡ ለሥራም፡ ትክክለኛና፡ ተስማሚ፡ የአሠራር፡ ሁኔታዎችና፡ ሥራም፡ እንዳያጣ፡ መብት፡ አለው።

፪/፡ እያንዳንዱ፡ ሰው፡ያላንዳች፡ ልዩነት፡ ማድረግ፡ ለአንድ፡ ዓይነት፡ ሥራ፡ እኩል፡ የሆነ፡ ደመወዝ፡ የማግኘት፡ መብት፡ አለው።

፫/፡ በሥራ፡ ላይ፡ ያለ፡ ሰው፡ ለእራሱና፡ ለቤተሰቡ፡ ለሰብዓዊ፡ ክብር፡ ተገቢ፡ የሆነ፡ ኑሮን፡ የሚያስገኝለትና፡ ካስፈለገም፡ በሌሎች፡ የኀብረሰብ፡ ደህንነት፡ መጠበቂያ፡ ዘዴዎች፡ የተደገፈ፡ ትክክለኛና፡ ተስማሚ፡ ዋጋውን፡ የማግኘት፡ መብት፡ አለው።

፬/፡ እያንዳንዱ፡ ሰው፡ ጥቅሞቹን፡ ለማስከበር፡ የሙያ፡ ማኀበሮችን፡ ለማቋቋምና፡ ማኀበርተኛ፡ ለመሆን፡ መብት፡ አለው።

አንቀጽ፡፳፬፤

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

እያንዳንዱ፡ ሰው፡ የዕረፍትና፡ የመዝናናት፡ እንዲሁም፡ በአግባብ፡ የተወሰኑ፡ የሥራ፡ ሰዓቶች፡ እንዲኖሩትና፡ በየጊዜው፡ የዕረፍት፡ ጊዜያትን፡ ከደመወዝ፡ ጋር፡ የማግኘት፡ መብት፡ አለው።

አንቀጽ፡፳፭፤

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

፩/፡ እያንዳንዱ፡ ሰው፡ ለእራሱና፡ ለቤተሰቡ፡ ጤንነትና፡ ደህንነት፡ ምግብ፣ ልብስ፣ ቤትና፡ ሕክምና፡ አስፈላጊ፡ የማኀበራዊ፡ ኑሮ፡ አገልግሎቶችም፡ ጭምር፡ የሚበቃ፡ የኑሮ፡ ደረጃ፡ ለማግኘት፡ መብት፡ አለው። ሥራ፡ ሳይቀጠር፡ ቢቀር፡ ቢታመም፡ ለመሥራት፡ ባይችል፡ ባል፡ ወይም፡ ሚስት፡ ቢሞት፡ ቢያረጅ፡ ወይም፡ ከቁጥጥሩ፡ ውጭ፡ በሆኑ፡ ምክንያቶች፡ መሰናከል፡ ቢገጥመው፡ ደህንነቱ፡ እንዲጠበቅለት፡ መብት፡ አለው።

፪/፡ ወላድነትና፡ ሕጻንነት፡ ልዩ፡ ጥንቃቄና፡ እርዳታ፡ የማግኘት፡ መብት፡ አላቸው፤ በጋብቻ፡ ወይም፡ ያለጋብቻ፡ የሚወለዱ፡ ሕጻናትም፡ የተመሳሳይ፡ የደህንነታቸው፡ መጠበቅ፡ መብት፡ አላቸው።

አንቀጽ፡፳፮፤

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

፩/፡ እያንዳንዱ፡ ሰው፡ የመማር፡ መብት፡ አለው። ትምህርት፡ ቢያንስ፡ ቢያንስ፡ በአንደኛ፡ ደረጃና፡ መሰረታዊ፡ ደረጃዎች፡ በነጻ፡ ሊሆን፡ ይገባል። የአንደኛ፡ ደረጃ፡ ትምህርት፡ መማር፡ ግዴታ፡ ነው። የቴክኒክና፡ የልዩ፡ ልዩ፡ ሙያ፡ ትምህርት፡ በጠቅላላው፡ የከፍተኛ፡ ደረጃ፡ ደግሞ፡ በችሎታ፡ መሠረት፡ ለሁሉም፡ እኩል፡ መሰጠት፡ አለበት።

፪/፡ ትምህርት፡ ለእያንዳንዱ፡ ሰው፡ ሁኔታ፡ ማሻሻያና፡ ለሰብዓዊ፡ መብቶችም፡ መሠረታዊ፡ ነጻነቶች፡ ክብር፡ ማዳበርያ፡ የሚውል፡ መሆን፡ አለበት። እንዲሁም፡ የተለያየ፡ ዘር፡ ወይም፡ ሃይማኖት፡ ባሏቸው፡ ሕዝቦች፡ መካከል፡ ሁሉ፡ መግባባትን፡ ተቻችሎ፡ የመኖርንና፡ የመተባበርን፡ መንፈስ፡ የሚያጠነክርና፡ የተባበሩት፡ መንግሥታት፡ ድርጅት፡ ሰላምን፡ ለመጠበቅ፡ የሚፈጽማቸው፡ ተግባሮች፡ እንዲስፋፋ፡ የሚያበረታቱ፡ መሆን፡ አለበት።

፫/፡ ወላጆች፡ ለልጆቻቸው፡ ለመስጠት፡ የሚፈልጉትን፡ ትምህርት፡ ለመምረጥ፡ የቅድሚያ፡ መብት፡ አላችው።፡

አንቀጽ፡፳፯፤

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

፩/፡ እያንዳንዱ፡ ሰው፡ በኀብረ፡ ሰቡ፡ የባህል፡ ኑሮ፡ በነጻ፡ መካፈልና፡ በኪነ፡ ጥበብ፡ ለመጠቀም፡ በሳይንስ፡ እርምጃና፡ በጥቅሞቹም፡ ለመሳተፍ፡ መብት፡ አለው።

፪/፡ እያንዳንዱ፡ ሰው፡ ከደረሰው፡ ማንኛውም፡ የሳይንስ፡ የድርሰትና፡ የኪነ፡ ጥበብ፡ ሥራ፡ የሚያገኘው፡ የሞራሉንና፡ የሃብት፡ ጥቅሞች፡ እንዲከበሩለት፡ መብት፡ አለው።

አንቀጽ፡፳፰፤

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

እያንዳንዱ፡ ሰው፡ በዚህ፡ ውሳን፡ ውስጥ፡ የተዘረዘሩት፡ መብቶችና፡ ነጻነቶች፡ በሙሉ፡ በተግባር፡ እንዲውሉ፡ ለሚደረግባቸው፡ የኀብረሰብና፡ የኢንተርናሽናል፡ ሥርዓት፡ የመጠቀም፡ መብት፡ አለው።

አንቀጽ፡፳፱፤

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

፩/፡ እያንዳንዱ፡ ሰው፡ የራሱ፡ ነጻነትና፡ ሙሉ፡ መሻሻል፡ በሚያገኝበት፡ ኀብረሰብ፡ ውስጥ፡ የሚፈጽማቸው፡ ግዴታዎች፡ ይኖሩበታል።

፪/፡ እያንዳንዱ፡ ሰው፡ በመብቶቹ፡ በነጻነቶቹ፡ በሚጠቀምበት፡ ጊዜ፡ የሚታገደው፡ የሌሎችን፡ መብቶችና፡ ነጻነቶች፡ በሚገባ፡ ለማሰከበር፡ ብቻ፡ በተደነገጉ፡ ሕጎችና፡ የግብረ፡ ገብነትን፡ የጠቅላላውን፡ ሕዝብ፡ ፀጥታና፡ ደህንነት፡ በዴሞክራቲክ፡ ማኀበራዊ፡ ኑሮ፡ ትክክለኛ፡ የሆነው፡ ተፈላጊ፡ ጉዳይ፡ ለማርካት፡ በተወሰነው፡ ብቻ፡ ነው።

፫/፡ እነዚህ፡ መብቶችና፡ ነፃነቶች፡ በማንኛውም፡ ሁኔታ፡ የተባበሩት፡ መንግሥታት፡ ድርጅት፡ መሰረት፡ ዓላማዎች፡ ተቃራኒ፡ በሆነ፡ መንገድ፡ ሊፈጸሙ፡ አይገባቸውም።

አንቀጽ፡፴፤

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
በዚህ ውሳኔ ከላይ የተዘረዘረው ሁሉ በዚሁ ውስጥ የተጠቀሱትን ማናቸውም መብቶች ወይም ነጻነቶች ለማበላሸት በታሰበ ማንኛውም ዓይነት ተግባር ለማዋል ወይም ድርጊትን ለመፈጸም ለማንኛውም መንግሥት ወይም ድርጅት ወይም ሰው የተባሉ አይተረጎሙም።